እንኳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ ለገባችበት ታላቅ ክብረ በዓል አደረሳችኊ

እንኳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ ለገባችበት ታላቅ ክብረ በዓል አደረሳችኊ። ይኽ ታላቅ የንግሥ በዓል እሑድ ታኅሣሥ 3/2014 ዓ.ም. በታላቋ የሊቃውንት ሥፍራ በዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም ከፍ ባለ ኹኔታ ይከበራል። ስለኾነም ኹላችኹም ሕዝበ ክርስቲያን በዕለቱ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት አጠገብ በምትገኘው በዚኽች ታላቅ ገዳም በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ ትኾኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።