ስልክ፡ +251 (11) 551 2136 / +251 (11) 551 5278
የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም
“ስምዒ ወለትየ ወርእዪ፣ ወአጽምዒ ዕዝነኪ፤ ርስዒ ሕዝበኪ ወቤተ አቡኪ፤ እስመ ፈተወ ንጉሥ ሥነኪ።” “ልጄ ሆይ ስሚ እዪም፤ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን የአባትሽንም ቤት እርሺ፤ ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና።” (መዝ ፵፬፥፲)
ደብረ መንክራት ሥዕል ቤት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን
“አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት” “ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ” (ቅዳሴ ማርያም)
የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ለአባታቸው ለዳግማዊ አጼ ምኒልክ ለመልካም ሥራቸው መታሰቢያ ይኾን ዘንድ ያሠሩት ገዳም ነው
የ2015 ዓ.ም. የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል በድምቀት ተከብሮ ውሏል
በገዳማችን በዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በድምቀት ተከብሮ ውሏል (06/08/2015 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ)።
ልዩ የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር ተከናወነ
በገዳማችን ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም እና ደብረ መንክራት ስዕል ቤት ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን ተዘጋጅቶ የነበረው ልዩ የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት መጋቢት 16/2015 ዓ.ም ተከናውኗል።
እንኳን ኪዳነምህረት ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችኹ!
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓለ ንግሥ በገዳማችን ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም ውስጥ በምትገኘው ደብረ መንክራት ስዕል ቤት ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት የካቲት 16/2015 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።
“ቴክኖሎጂ እና የመገናኛ ብዙሃን ሚና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ዐውደ ጥናት
የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም ተግባቦት ክፍል፣ ከመሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት እና ‘አጥቢያ ዶት ኮም’ ከተባለ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለቤተክርስቲያን ከሚያቀርብ ዓለምአቀፍ ተቋም ጋር በመተባበር “ቴክኖሎጂ እና የመገናኛ ብዙሃን ሚና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ዐውደ ጥናት ትናንት ጥር 14/2015 ዓ.ም ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም ተከናወነ።
ቪድዮ ሪፖርታዥ – የ2014 ዓ.ም. የቀዳም ሥዑር ገብረ ሰላም ማሕሌታዊ ሥርዐት