በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/ የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ገዳሙ
  • ስብከተ ወንጌል
  • መንፈሳዊ ት/ቤት
  • ሰንበት ት/ቤት
  • ቤተ መዘክር
  • ያግኙን
  • Menu Menu

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት መታሰቢያ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት መታሰቢያ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በአዲስ አባባ ከተማ፤ ቤተ መንግሥት አጠገብ በምትገኘው፤ ጥንታዊና ልዮ የበረከት ቦታ በሆነችው፤  በዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም እና ደብረ መንክራ ስዕል ቤት ኪዳነ ምህረት ገዳም ታህሣስ 3/2014 ዓ.ም. በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ፡፡ በዕለቱም ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የገዳሟ ሊቃወንት፣ ታላላቅ አባቶችና እናቶች፣ እንዲሁም እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን በመገኘት በዓሉን አክብረዋል፡፡

ይህ ቀን የታላቁ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ (ወስመ ጥምቀቱ ሣሕለ ማርያም) በሞተ ሥጋ ያንቀላፉበት 108ኛ የሙት ዓመት መታሰቢያ እንደመሆኑም፡ መካነ መቃብራቸው በሚገኝበትና ለመታሰቢያቸው በተሰራው በዚሁ ገዳም ጸሎተ ፍትሀት ተከናውኖላቸዋል፡፡ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ልጃቸው ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ (ወስመ ጥምቀታ አስካለ ማርያም) የአባታቸው መልካም ስራ ይዘከርበት ዘንድ ይህን ገዳም በ1910 ዓ.ም. በጸሎትና በትጋት እንዲመሠረት አድርገዋል፡፡

ዳግመኛም ይህ ቀን የእምዬ ምኒልክ የጦር አበጋዝና የቅርብ ወዳጅ የሆኑት፣ ይህ ገዳም ሲመሠረት በርካታ ንብረታቸውን ለገዳሙ ማቋቋሚያ ያበረከቱት የርዕሰ መኳንንት፣ ፊታውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ (ወስመ ጥምቀቱ ኃብተ ጊዮርጊስ) ዕለተ ዕረፍት ነው፡፡

የእመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤትና በረከት ከሁላች ጋር ይሁን አሜን
ታህሣስ 3/2014 ዓ.ም.

በፎቶ ይመልከቱ

Previous Previous Previous Next Next Next
123456789101112
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail

በፌስቡክ ያግኙን

©በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ቁሳቁሶችና ምግቦች ማሰባሰቢያ Link to: ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ቁሳቁሶችና ምግቦች ማሰባሰቢያ ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ቁሳቁሶችና ምግቦች ማ... Link to: ስለ ታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም Link to: ስለ ታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም ስለ ታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም
Scroll to top Scroll to top Scroll to top