እንኳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቃል ኪዳን ለተቀበለችበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል ኹላችንንም አደረሰን!

“ይቤላ ለእሙ ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስ ኪዳነ ምሕረት፣
ዘተአመነኪ ከመ አድኅን ዘተአመነኪ መሐልኩ ለኪ በርእስየ።”

ትርጉም:
ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ማርያምን አላት ‘ኪዳነ ምሕረት የታመነሽን አድንልሽ ዘንድ በራሴ ምዬልሻለኁ። እምልልሻለኁ።’

እንኳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቃል ኪዳን ለተቀበለችበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል ኹላችንንም አደረሰን! በዓሉ በገዳማችን በምትገኘው ደብረ መንክራት ስዕል ቤት ኪዳነምህረት (የቀድሞዋ የዳግማዊ ምኒልክ ጸሎት ቤት) እየተከበረ ይገኛል።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎትና ምልጃ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!