ስልክ፡ +251 (11) 551 2136 / +251 (11) 551 5278
የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም
“ስምዒ ወለትየ ወርእዪ፣ ወአጽምዒ ዕዝነኪ፤ ርስዒ ሕዝበኪ ወቤተ አቡኪ፤ እስመ ፈተወ ንጉሥ ሥነኪ።” “ልጄ ሆይ ስሚ እዪም፤ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን የአባትሽንም ቤት እርሺ፤ ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና።” (መዝ ፵፬፥፲)
ደብረ መንክራት ሥዕል ቤት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን
“አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት” “ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ” (ቅዳሴ ማርያም)
የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ለአባታቸው ለዳግማዊ አጼ ምኒልክ ለመልካም ሥራቸው መታሰቢያ ይኾን ዘንድ ያሠሩት ገዳም ነው
ፎቶ ሪፖርታዥ – የ2014 ዓ.ም. ስቅለት በዓል
ቪድዮ ሪፖርታዥ – የ2014 ዓ.ም. ስቅለት በዓል
ፎቶ ሪፖርታዥ – የ2014 ዓ.ም. ጸሎተ ሀሙስ
እንኳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቃል ኪዳን ለተቀበለችበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል ኹላችንንም አደረሰን!
በዓሉ በገዳማችን በምትገኘው ደብረ መንክራት ስዕል ቤት ኪዳነምህረት (የቀድሞዋ የዳግማዊ ምኒልክ ጸሎት ቤት) እየተከበረ ይገኛል።
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎትና ምልጃ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!
ዓመታዊ የንግሥ በዓል በታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት መታሰቢያ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በአዲስ አባባ ከተማ፤ ቤተ መንግሥት አጠገብ በምትገኘው፤ ጥንታዊና ልዮ የበረከት ቦታ በሆነችው፤ በዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም እና ደብረ መንክራ ስዕል ቤት ኪዳነ ምህረት ገዳም ታህሣስ 3/2014 ዓ.ም. በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ፡፡ በዕለቱም ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የገዳሟ ሊቃወንት፣ ታላላቅ አባቶችና እናቶች፣ እንዲሁም እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን በመገኘት በዓሉን አክብረዋል፡፡