ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ቁሳቁሶችና ምግቦች ማሰባሰቢያ

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሣን ንፅህተ ንፁሐን ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ወደቤተመቅደስ ለገባችበት አመታዊ ክብረ በዓል አደረሣችሁ እያልን እሁድ ታህሣስ 3/2014 ዓ.ም ቀጠሮአችሁን በታላቋ ገዳም በዳግማዊ ምኒልክ መታሠቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም እንድታደርጉ እየጋበዝን

  1. የበዓሉን በረከት ለመሣተፍ ስትመጡ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ እንዳትረሡ
  2. በሀገራችን በተከሠተው ጦርነት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ከጎናችሁ አለን፤ ወገን አላችሁ ለማለት እንደክርስቲያንም ይህን የበጎ ስራ በረከት ለመሻማት ወደክብረ በዓሉ ስትመጡ

*ደረቅ ምግቦች – ቶሎ የማይበላሹ
*አልባሣት
* የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ
* ለህፃናት ሳይበላሹ ሊደርሱ የሚችሉ ምግቦች ይዛችሁ እንድትመጡ በእመቤታችን ስም እንጠይቃለን

የገዳሟ አድራሻ: 4 ኪሎ ታላቁ ቤተ መንግስት ወይም ግቢ ገብርኤል ጎን