በገዳማችን በዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በድምቀት ተከብሮ ውሏል (06/08/2015 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ)።

ምስባክ ዘስቅለት ዘሠለስቱ ሰዓት

ግፍዖሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍዑኒ
ጽብኦሙ እግዚኦ ለእለ ይጸብኡኒ
ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍዑኒ

ትርጉም።
አቤቱ የሚበድሉኝን በድላቸው።
የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው።

ምስባክ ዘስቅለት ዘስድስቱ ሰዓት

ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ።
ወኈለቁ ኵሎ አዕፅምትየ።

ትርጉም።
እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ
አጥንቶቼንም ኹሉ ቆጠሩ።

ምስባክ ዘስቅለት ዘተስዓቱ ሰዓት

ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ።
ወአስተዩኒ ብሒአ ለጽምዕየ።

ትርጉም።
በመብሌ ውስጥ ሐሞት ጨመሩ።
ለጥማቴም ሆምጣጤን አጠጡኝ።