በኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/ የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ገዳሙ
  • ስብከተ ወንጌል
  • መንፈሳዊ ት/ቤት
  • ሰንበት ት/ቤት
  • ቤተ መዘክር
  • ያግኙን
  • Menu Menu

እንኳን ኪዳነምህረት ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችኹ!

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓለ ንግሥ በገዳማችን ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም ውስጥ በምትገኘው ደብረ መንክራት ስዕል ቤት ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት የካቲት 16/2015 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል። በገዳሟ ሥርዓት መሠረት በዓቢይ ጾም ወቅት ከበሮ አይመታምና፤ ከማህሌቱ ጀምሮ እስከ አውደ ምህረቱ ያለው መዝሙር ከበሮ ሳይመታ፣ ጸናጽል ሳይንጸለጸል በመቋሚያ ብቻ በመዘመም ስብሐተ እግዚአብሔርን በማድረስ ተከብሯል።

ደብረ መንክራት ስዕል ቤት ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን የንጉሠ ነገሥቱ የአጼ ዳግማዊ ሚኒልክ ጸሎት ቤት የነበረች፤ ኋላም ታቦተ ኪዳነ ምህረትን አስገብተው የነገሥታቱና የመኳንንቱ ማስቀደሻ ሆና የኖረች ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ነች።

መዝሙራት

ኪዳንኪ ኮነ፤ ለኃጥአን ተስፋነ ኪዳንኪ ኮነ።

ትርጉም፡ እመቤታችን ሆይ ቃል ኪዳንሽ ለኛ ለኃጥአን ተስፋችን ኾነ።

ክንፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር፣ ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤
አንቲ ምሥራቅ ወወልድኪ ፀሀየ ጽድቅ፣ ምሥራቅ ታዕካ ነገሥት

ትርጉም፡ ክንፎችሽ በብር ያጌጡ፣ ጎኖችሽ በወርቅ አመልማሎ የተሰሩ፤
አንቺ ምስራቅ(የጸሐይ መውጫ) ነሽ ልጅሸም እውነተኛ ፀሐይ፤ የፀሐይ መውጫ ታዕካ ነገሥት

ጼጥሮስኒ ይቤ በውስተ ውግዘት ምድር ሰናይት ኢትዮጵያ ወአኮ ከመ ምድረ ሮም፤
ምድር ሰናይት ደብረ መንክራት እንተ ዘልፈ ይሔውጻ እግዚአብሔር በማርያም ድንግል እም ዓመት እስከ ርእሰ ዐውደ ዓመት፤

ትርጉም፡ ጴጥሮስ እንዲኽ አለ ኢትዮጵያ መልካም ምድር ናት እንደሮም ምድርም አይደለችም፤ ኢትዮጵያ ውብ መልካም ናት ሲል ጼጥሮስ በውግዘቱ ውስጥ እንደተናገረ፡፡
ከዓመቱ መነሻ እስከ ዓመቱ ዙሪያ ራስ (ከዓመቱ መዠመሪያ እስከ ዓመቱ ፍጻሜ) በድንግል ማርያም ረድኤት እግዚአብሔር ዘወትር የሚጎበኛት ደብረ መንክራት መልካም ናት፡፡

የበዓሉ አከባበር በፎቶ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail

በፌስቡክ ያግኙን

©በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: “ቴክኖሎጂ እና የመገናኛ ብዙሃን ሚና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ዐውደ ጥናት Link to: “ቴክኖሎጂ እና የመገናኛ ብዙሃን ሚና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ዐውደ ጥናት “ቴክኖሎጂ እና የመገናኛ ብዙሃን ሚና ለቤተ ክርስቲያን... Link to: ልዩ የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር ተከናወነ Link to: ልዩ የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር ተከናወነ ልዩ የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር ተከናወነ
Scroll to top Scroll to top Scroll to top